ከ2 አመታት በሁዋላ በኢትዮጵያ አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል


ጠ/ሚንስትር አብይ የተለያዩ ሃይሎችን ወቀሱ
(ERF) ጠ/ሚ አብይ አህመድ 2ኛውን የለውጥ አመት ለመዘከር ባወጡት ጽሁፍ ለኢትዮጵያ አለመረጋጋት ተጠያቂ ናቸው ያሉዋቸውን ሃይሎች ወቅሰው፣ ከሁለት አመት በሁዋላ ግን አንጻራዊ ሰላም ማስፈን ተችሏል ብለዋል።
ጠ/ሚ በጽሁፋቸው ” ኃላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች ንግግር ወንድም እህቶቻችንን የተቀጠፉበት፤ በትንሽ በትልቁ የህግ የበላይነት ያበቃለት፣ ኢትዮጵያም ያከተመላት እንዲመስል ተደጋጋሚ የጥፋት ርምጃዎች የተካሄዱበት ወቅት አልፎ ከሞላ ጎደል ወደ ሰላማችን ተመልሰናል፡፡” ብለዋል። ሃላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች ንግግር ያሉት የኦፌኮው አቶ ጀዋር መሃመድ “ተከብቤአለሁ ድረሱልኝ” ማለቱን ተከትሎ የደረሰውን ጥፋት ለማስታወስ የተጻፈ ተደርጎ ተወስዷል።
በሶማሊ ክልልም እስካፍንጫው የታጠቀው ጨካኝ ሃይል ክልሉን የመገንጠል አላማ የነበረው ቢሆንም ማክሸፍ ተችሏል ሲሉ ጠ/ሚ ጽፈዋል።
“በወለጋ እና በሌሎች የምእራብ ኦሮሚያ ክፍሎች ላይ የጥፋት በትራቸውን አሳርፈው ባንክ እየዘረፉ፣ ሰው እየገደሉ፣ ቤት እያቃጠሉ፣ መንገድ እየዘጉ፣ ትምህርት ቤት እየዘጉ ነዋሪውን እያማረሩ የነበረበት፤ ከገጠር ቀበሌዎች አልፎ እንደ ነቀምት፣ ጊምቢ እና ሻምቦ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ውስጥ መንግስታዊ መዋቅርን ለማፈራረስ የተንቀሳቀሰበት፤ የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎች ያለወታደራዊ አጀብ የሚያስቸግሩበት ጊዜያትን አስተናግደናል፡፡”በማለት የኦነግ ሸኔን ድርጊት ኮንነዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ ይህም ጊዜ አልፏል ቢሉም አሁንም ድረስ ባለስልጣናት በኦነግ ሸኔ ወታደሮችና ደጋፊዎች እየተገደሉ ነው።

“በአንድ ቀን በአማራ ክልል ጠንካራ ጓዶቻችንን በግፍ አጥተን፤ በአዲስ አበባ ተወዳጅ የጦር መሪዎቻችን ተገድለው፤ ውጥረቱ ለድፍን ኢትዮጵያ ተርፎ የነበረበት ጊዜ አልፏል፡፡” ሲሉ የሰኔ 15ቱን የብ/ጄ አሳምነው ጽጌን ድርጊትና በጀኔራል ሳዕረ መኮንን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውስተዋል።

“ዜጎች ኢትዮጵያ ልትበታተን ትችላለች በሚል ስጋት ውስጥ እንዲቆዩ የሆነበት አስጨናቂ ጊዜን ተረማምደናል፡፡” የሚሉት ጠ/ሚኒስትሩ ያንን ጊዜ እንደተሸጋገርነው አሁንም የኮሮናን ወረርሽኝ እንከላከለዋለን ብለዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: