በኢትዮጵያ የተገኘው መድሃኒት ተስፋ ሰጪ ነው

(ERF) የኢትዮጵያ የባህል መድሃኒት አዋቂዎች ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሰሩት የኮሮና በሽታ መድሃኒት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ዘ ኢስት አፍሪካን  ዘግቧል።

ዘ ኢስት አፍሪካን መድሃኒቱን የቀመሙትን ባለሙያዎች አነጋግሮ እንደዘገበው መድሃኒቱ የአለም የጤና ድርጅት ባወጣቸው መስፈርቶች መሰረት የተለያዩ ደረጃዎችን አልፎ የክሊኒክ ሙከራዎችን ለማድረግ ተቃርቧል። የክሊኒክ ሙከራው የሚደረገው በሰዎች ላይ ይሆናል ማለት ነው። ሙከራውም በውጭ አገር በሚገኙ ላብራቶሪዎች መመርመሩም ተዘግቧል።

የመድሃኒቱ ቀማሚዎች እንደተናገሩት መድሃኒቱ ምንም አይነት የመርዛማነት ጸባይ የለውም።  መድሃኒቱ የክሊኒካል ሙከራዎችን አልፎ በሚቀጥሉት 3 ወራት ውስጥ ፈዋሽነቱ ተረጋግጦ ይፋ ይደረጋል ብለው የመድሃኒት ቀማሚዎች ያምናሉ። ፈዋሽነቱን በተመለከተ ግን ጥርጣሬ የላቸውም።

የምርምሩ ስራ እየተጠናቀቀ በመሆኑ መድሃኒቱን በብዛት ለማምረት ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሆነም ዘ ኢስት አፍሪካ ዘግቧል።

የጤና ጥበቃና የኢኖቬሽን ሚኒስቴሮች መረጃውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ደስታና ተስፋ መፍጠሩ ይታወቃል። አንዳንድ ወገኖች ግን መንግስት ጉዳዩን ያለ ወቅቱ ይፋ ማድረጉ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የሚደረገውን ሙከራ ያደናቅፈዋል በሚል ትችት ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

የኢትዮጵያ የባህል መድሃኒት አዋቂዎች የቀመሙት መድሃኒት ፈዋሽነቱ ከተረጋገጠ ለአለም ህዝብ ታላቅ የምስራች ይዞ የሚመጣ ነው። በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ ኩባንያዎች ለበሽታው መድሃኒት ለመስራት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካላቸውም። ይሁን እንጅ የአለም የጤና ድርጅት ከዚህ ቀደም የነበሩ የወባና የኤች አይ ቪ መድሃኒቶች የክሊኒካል ሙከራ እንዲደረግባቸው ወስኖ በ74 አገራት ሙከራዎች የተደረጉ ነው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: