(ERF) ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ሩስያ ሰራሽ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን መታጠቋን የስዊድኑ ስቶክሆልም አለማቀፍ የሰላም ምርምር ተቋም አስታውቋል።
ጥናቱ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ አራት 96K9 Pantsyr-S1 Mobile air defense system እንዲሁም አንድ መቶ የሚሆኑ 57E6 SAM missile ከሩስያ መግዛቷን አመልክቷል።

አየር ሃይሉን ለማዘመንም ስድስት ከጀርመን መንግስት የተገዙ የበረራ ማስተማሪያ አውሮፕላኖች ተገዝተዋል።
ኢትዮጵያ አብዛኛውን የጦር መሳሪያዎቿን የገዛችው ከሩስያ ሲሆን፣ ከ71 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጋለች።
ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎቹ በአብዛኛው የአየር ጥቃትን ለመከላከል ተብለው የተገዙ ናቸው።
ከምስራቅ አፍሪካ አገራት ጋር ሲተያይ ለጦር መሳሪያ ግዢ ከፍተኛ ወጪ ያወጣችው ኢትዮጵያ ስትሆን፣ ኬንያ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ግብጽ በእያመቱ ለጦር መሳሪያ ግዢ ከምታወጣው ወጪ ጋር ሲተያይ የኢትዮጵያ ወጪ አነስተኛ ነው።

Leave a Reply