የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኛ ማህበሩን መሪ አባረረ

ከፍተኛ ውዝግብ ተፈጥሯል

(ERF) በኮሮና ቫይረስ የተነሳ አየር መንገዱ ከ 200 እስከ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ኪሳራ ያጋጠመው መሆኑን ተከትሎ ሰራተኞች ያለ ክፍያ ለተወሰነ ጊዜ እረፍት እንዲወስዱ፣ ይህን በማይቀበሉ ሰራተኞች ላይ ግን የማባረር እርምጃ እንደሚወስድ ማሳወቁን ተከትሎ በሰራተኞችና በስራ አስፈጻሚው መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቷል። ሰራተኞቹ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ትክክል አይደለም ይላሉ። ዋና ስራ አስፈጻሚው የሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበር የሆኑትን ካፒቴን የሽዋስ ፋንታሁንን የስራ ውል ያቋረጠ ሲሆን፣ ሌሎች የሰራተኛው ማህበሩ አመራሮች ድርጊቱን በጽኑ አውግዘዋል። ሰራተኞቹ እርምጃው ሆን ተብሎ ሰራተኞውን ለማሸማቀቅ ኮሮናን ሰበብ አድርጎ የተወሰደ የተለመደ አሰራር ነው በማለት ገልጸዋል።

የሰራተኛ ማህበራቱ አየር መንገዱ ገቢው የቀነሰበት መሆኑ ትክክል መሆኑን ቢቀበሉም፣ ሰራተኞችን የሚያስቀንስበት ወይም ያለክፍያ የሚያሰራበት ሁኔታ ላይ ነው ብለው አያምኑም። አየር መንገዱ ከሰራተኞች ጋር ተነጋግሮ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን መተማመን ላይ ከተደረሰ ሰራተኞች አስፈላጊውን መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸው ይገልጻሉ። ይሁን እንጅ ሌሎች አየር መንገዶች አድርገዋል በሚል ብቻ የሰራተኞችን ደሞዝ ማስቀረት ትክክል አለመሆኑን ማህበሩ ገልጿል። ሰራተኞች ፈቃዳቸው ሳይጠየቅ ያለደሞዝ እረፍት እንዲወጡ ማድረግም ትክክል አይደለም ይላሉ የማህበሩ መሪዎች ። ከሁሉም በላይ ከዚህ ቀደም ይደረግ እንደነበረው ለሰራተኞች መብት የሚቆሙ የማህበሩን አመራሮች በማባረር ለማሸማቀቅ መሞከር ተገቢ ያልሆነ ሁዋላ ቀር እርምጃና ሰራተኞችን እንደ ባሪያ ከመቁጠር የመጣ አየር መንገዱንም በሂደት የሚጎዳ እርምጃ ነው ይላሉ።

በአቶ ተወልደ ገ/ማርያም የሚመራው አየር መንገድ ኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱ በፊት በትራፋማነቱና በሚያሳየው ፈጣን እድገት ተጠቃሽ የነበረ ቢሆንም፣ ከሰራተኞች አያያዝ ጋር በተመለከተ ግን ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል። አየር መንገዱ የውጭ አገር አብራሪዎችን ከኢትዮጵያውያን በተለየ የሚያይበትና የሚይዝበት ሁኔታ ብዙ ሰራተኞችን ሲያበሳጭ ቆይቷል። የሰራተኞቹ የኑሮ ሁኔታ አለመሻሻል፣ በሚሰሩት ስራ ልክ ከፍያ የማይፈጸምላቸው መሆኑ እንዲሁም ሃሳባቸውን ሲገልጹ ፈጣን እርምጃ የሚወስድባቸው መሆኑን በማንሳት አንዳንዶች ድርጅቱን ጥለው እስከመውጣት ደርሰዋል። ሌሎች ደግሞ አጋጣሚውን ሲጠብቁ ቆይተዋል።

የኮቪድ19 ወረርሽኝ እንደተነሳ አየር መንገዱ በረራ ባለማቆሙ በአመራሩ ላይ ከፍተኛ ውርጅብኝ ሲደርስበት ቆይቷል። ዘግይቶም ቢሆን በተለይም ሌሎች አገሮች አየር መንገዱ ወደ አገራቸው እንዳይገባ እየከለከሉ በመምጣታቸው ወደ 87 አገራት የሚያደርገውን በረራ ለመሰረዝ ተገዷል። ያም ሆኖ ግን አየር መንገዱ አሁንም ቢሆን ወደ አውሮፓና አሜሪካ የሚያደርጋቸውን አንዳንድ በረራዎች እና እቃ የማጓጓዝ ስራውን አላቆመም።

እስካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ የአየር መንገድ ሰራተኛ ይኑር አይኑር አይታወቅም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን ያለ ክፍያ ለእረፍት እንዲወጡ የወሰነውን ውሳኔ ተግባራዊ ካደረገው በርካታ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ሊጎዱ ይችላሉ።

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የአየር መንገዱ ገቢ መቀነስ በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ላይ ጫና መፍጠሩን በፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ላይ በጻፉት ጽሁፍ አመላክተው ነበር።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰባቸው ተቋማት መካከል አየርመንገዶች በግንባር ቀድምነት ይጥቀሳሉ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: