የሙቀት መጨመር የኮሮና ስርጭት ይገታ ይሆን?

(ERF) ስለኮሮና ቫይረስ ከሚታወቀው ይልቅ የማይታወቀው ይበልጣል። ምክንያቱ ደግሞ ቫይረሱ አዲስ ስለሆነ ነው። ከተወሰኑ ወራት በሁዋላ ስለቫይረሱ ጠባይ ከሚታወ ዛሬ ከሚታወቀው በላይ ይታወቃል። ያን ጊዜ መድሃኒትም ሆነ ክትባት ለማዘጋጀት ከባድ እንደማይሆን ይገመታል።

ኮሮናን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች ይጠየቃሉ። ተደጋግመው ከሚቀርቡ ጥያቄዎች መካከል አንዱ፣ የአየር ጸባይ በኮሮና ስርጭት ላይ የሚኖረውን ተጽዕኖ የተመለከተ ነው። በአጠቃላይ ሲታይ ሁለት መላ ምቶች አሉ። አንደኛው መላ ምት፣ እንደ ማንኛውም የጉንፋን አይነት፣ የኮቪድ19ኝ ስርጭት፣ በሞቃታማ የአየር ጸባይ እየቀነሰ ይሄዳል የሚል ነው። ሌላው መላ ምት ደግሞ ኮቪድ19 እስካሁን ከሚታወቁት የቫይረስ አይነቶች የተለየ በመሆኑ በአየር ጸባይ የተነሳ ስርጭቱ አይቀንስም የሚል ነው።

የኮሮና ቫይረስ በአሁኑ ሰዓት ሞቃታማ የአየር ጸባይ ባላቸው አገራት፣ ለምሳሌ በኢትዮጵያ፣ ስርጭቱ አነስተኛ ነው። የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ የሚታየው ቀዝቃዛና መካከለኛ የአየር ጸባይ ባላቸው አገራት ነው። ይህንን ሁኔታ ስናይ በእርግጥም የአየር ጸባይ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ ይመስላል። ይሁን እንጅ ሞቃታማ በሆኑ የአረብ አገራት የቫይረሱ ስርጭት አሁንም በአጻራዊነት ከፍተኛ የሚባል ነው። ይህ ማለት ቫይረሱ በሁሉም የአየር ጸባይ ላይ የመኖር አቅም አለው ማለት ነው። እንዲህ ከሆነ ታዲያ ጥያቄው ቫይረሱ በሞቃታማ የአየር ጸባይ ይኖራል አይኖርም ሳይሆን፣ የቫይረሱ የስርጭት ፍጥነት በሁሉም የአየር ጠባዮች አንድ አይነት ነውን የሚለው ይሆናል ማለት ነው።

ዘ ጋርዳያን ኤፕሪል 5፣ 2020 ባወጣው ጽሁፍ ላይ እንደገለጸው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ የሆኑት እንደ HCoV-NL63, HCoV-OC43 and HCoV-229E – የመሳሰሉት ቫይረሶች በየካቲት ወር ከፍተኛ የመሰራጨት ባህሪ የሚያሳዩ ሲሆን፣ በሙቀት ጊዜ ደግሞ ስርጭታቸው ይቀንሳል። ይህ ማለት የኮሮቫ ቫይረስ ዝርያዎች ስርጭት ከአየር ጸባይ መለዋወጥ ጋር እንደሚያያዝ የሚያሳይ ነው። ይሁን እንጅ ኮቪድ19 ከእነዚህ የቫይረሱ አይነቶች ጋር ያለው ዝምድናና ልዩነት ገና በውል አልታወቀም። በዚህም የተነሳ ሳይንቲስቶች የአየር ጸባይ መለዋወጥ በቫይረሱ ስርጭት ላይ ስላለው ተጽዕኖ በእርግጠኝነት ለመናገር አይደፍሩም።

ቪሮሎጂስት ሚካኤል ስኪነር፣ የአየር ጸባይ ለውጥ በቫይረሱ ስርጭት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ይኖራል ብሎ እንደሚያምን ይናገራል። ነገር ግን ማህበራዊ መራራቅ የሚፈጥረውን ያክል ተጽዕኖ ይፈጥራል ብሎ አያምንም። ሙቀት መጠነኛ ጠቀሜታ ሊኖረው ይችላል፤ የራስን እንቅስቃሴ የመግታትን ያክል (self-isolation) ጥቅም ግን አይስገኝም ።” ይላል።

 የኮቪድ19 ባሀሪ ከአየር ጸባይ ጋር ያለው ግንኙነት ገና በውል ባይታወቅም፣ የሰዎች የተፈጥሮ መከላከያ በሙቀት ጊዜ እየጨመረ እንደሚሄድ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህም ሰውነታችን ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችለውን ነጭ የደም ሴል በብዛት እንዲያመርት ያስችለዋል።

በኢትዮጵያ አሁን ያለው የአየር ጸባይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እየረዳ ይሁን አይሁን ገና አልታወቀም። በሚቀጥሉት 2 ሳምንታት የቫይረሱ ስርጭት አሁን እንደሚታየው አነስተኛ ከሆነ፣ የኮሮና ስርጭትና የአየር ጸባይ ቀጥተኛ ዝምድና ሊኖራቸው እንደሚችል የተሻለ ግምት ማሳደር ይቻላል። በተለይ ስርጭቱ በአውሮፓና በአሜሪካ እየቀነሰ የሚሄድ ከሆነ፣ ግምቱም እየሰፋ ይሄዳል። ለማንኛውም ግን የጤና ባለሙያዎች የሚመክሩትን ምክር ሳያሳልሱ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: