ፕ/ት ትራምፕና ጓደኞቻቸው ዶ/ር ቴዎድሮስን ለማባረር ቆርጠው ተነስተዋል

ፕ/ት ትራምፕ እና የአሜሪካን ሪፐብሊካን አባላት የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ለማባረር ቆርጠው ተነስተዋል። ትራምፕ ለጤና ድርጅቱ የምንሰጠውን በጀት እንቀንሳለን ብለዋል። “የጤና ድርጅቱ ለቻይና ያደላል፣ በቂ ዝግጅት እንድናደርግ አልመከረንም፤ ድንበራችን እንዝጋ ስንለውም አያስፈልግም ብሎናል” የሚል ወቀሳ ያሰማሉ።

የሪፐብሊካኑ ሴናተር ሊንድሰይ ግርሃም በበኩላቸው አሁን ባለው አመራር ለአለም የጤና ድርጅት የሚሰጥ ድጋፍ እንደማይኖር ገልጸዋል። ምክንያታቸው ደግሞ አመራሩ አታላይ፣ ዘገምተኛና የቻይና ወኪል ነው የሚል ነው።

ሌላው የሪፐብሊካን ሴናተር ማርኮ ሩብዮ ደግሞ ቤንጂንግ የአለም የጤና ድርጅትን ተጠቅማ አለምን በማሳሳቷ ዶ/ር ቴዎድሮስ ስልጣን ሊለቁ ይገባል ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ ግን ይህንን ውንጀላ አይቀበሉትም። የጤና ድርጅቱ በዶ/ር ቴዎድሮስ አመራር ታላቅ ስራ እንደሰራ ይናገራሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ከተሾሙ በሁዋላ አለም ኮሮናን ለመከላከል በጋራ እንዲነሳ በማስተባበር የሰሩትን ስራ እንዲሁም ኢቦላን ለማጣፋት የተደረገውን ዘመቻ በማንሳት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

አልጀዚራ እንደዘገበው፣ በአሜሪካኖች በኩል የሚቀርበው ክስ ወቅቱን ያልጠበቀ ነው። ጀርሚይ ኮንያዲክ የተባሉ የሴንተር ፎር ግሎባል ዴቭሎፕመንት ሃላፊ ፣ የጤና ድርጅቱና የአሜሪካ መንግስት በዚህ ሰዓት ማድረግ የሌለባቸው ነገር ቢኖር እርስ በርስ መጣላት ነው ብለዋል።

“እንዲህ አይነቱ ውንጀላ በሽታውን በበቂ ሁኔታ እንዳትከላከል ትኩረትክን ያስትሃል።”

“የአለም የጤና ድርጅት ጥር መጨረሻ ላይ በቂ መረጃ አቅርቧል። ይህንን ተጠቅሞ እርምጃ መውሰድ ይቻል ነበር። የጤና ድርጅቱ ከትራምፕ አስተዳደር በተሻለ የቫይረሱን አደገኛነት ተረድቶ አሳውቋል። ለትራምፕ መንግስት ቀርፋፋ ምላሽ የጤና ድርጅቱ መወቀስ ያለበት አይመስልኝም።” ሲሉ ባለሙያው ገልጸዋል።

የአለም የጤና ድርጅት ወቅታዊ መመሪያ አገሮች ድንበራቸውን እንዲዘጉ ወይም ጉዞ እንዲሰርዙ አያስገድድም።ይሁን እንጅ አገሮች በመሰላቸው መንገድ የራሳቸውን የግል እርምጃ ወስደዋል።

የአለም የጤና ድርጅት ጃንዋሪ 30 ላይ አሳሳቢ ወረርሽኝ መከሰቱን በመግለጽ አገሮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።  ከአንድ ወር በሁዋላ  ግን ፕ/ት ትራምፕ “አሜሪካ ውስጥ የኮሮና ቫይረስን ተቆጣጥረነዋል” ብለው መግለጫ ሰጥተዋል። እንደገና መልሰው ከአንድ ወር ከ 13 ቀናት በሁዋላ ብሄራዊ የአደጋ ጊዜ አውጀዋል። ይህ የፕ/ት ትራምፕን አመራር ድካማነት የሚያሳይ ነው።

የአፍሪካ ህብረት ዋና ጸሃፊ “የአሜሪካ መንግስት በአለም የጤና ድርጅት ላይ የጀመረው ዘመቻ እንዳስገረማቸው ገልጸው፣ ህብረቱ  ሙሉ በሙሉ ከዶ/ር ቴዎድሮስ ጎን እንድሚቆም ገልጿል።

የአሜሪካ መንግስት በአለም የጤና ድርጅት ላይ የሚያሰማው ውንጀላ ኢትዮጵያውያንንም ከሁለት ከፍሏቸዋል።ዶ/ር ቴዎድሮስ የጤና ጥበቃ ሚ/ር በነበሩበት ወቅት የሰሩዋቸውን ጥፋቶች እያነሱ ከአሜሪካ ሪፐብሊካን ጎን ቆመው ከስልጣን ይውረዱ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፣ ግለሰቡ በጤና ድርጅቱ ውስጥ በሚሰሩት ስራ ሲመዘኑ ከማንም የተሻለ እንጅ ያነሰ ስራ ባለመስራታቸው ሃላፊነታቸውን ሊለቁ አይገባም የሚሉም አሉ።

አሜሪካኖች ከቻይና ጋር በገቡት እኔ እበልጥ እበልጥ ውዝግብ እንዲሁም የአሜሪካ መንግስት በሽታውን ለመቆጣጠር ያሳየውን ደካማነት ለመሸፋፈን የአለም የጤና ድርጅትን እንደ ሰበብ እየተጠቀመ ነው የሚል ክስ ከእያቅጣጫው ይቀርባል።

አሜሪካ ለአለም የጤና ድርጅት ከፍተኛ ባጀት ከሚመድቡ አገራት መካከል ቀዳሚዋ ናት። የአሜሪካ አቋም በጤና ድርጅቱ አሰራር ላይ የሚያመጣው ጉዳት ቀላል አይባልም። ፕ/ት ትራምፕ ዶ/ር ቴዎድሮስ ከስልጣን እንዲወርዱ፣ ካልወረዱ ግን በጀት እንደሚቀንሱ ጠንካራ አቋም የሚይዙ ከሆነ ዶ/ር ቴዎድሮስ ቦታቸውን በግፊት ሊለቁ ይችላሉ።

ዶ/ር ቴዎድሮስ በአመራራቸውም ሆነ በመግለጫ አሰጣጣቸው የተለያዩ ታዋቂ ሰዎች አድናቆታቸውን ገልጸውላቸዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስም ሆነ የጤና ድርጅቱ ስለሚቀርብባቸው ውንጀላ እስካሁን መልስ አልሰጡም።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: