ጎንደርን የሚያስለቅሰው ፋኖ ወይስ መንግስት?

ሰሞኑን በጎንደር በፋኖ አባላት ላይ መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ብዙ አስተያየቶች እየቀረቡ ነው። አንዳንዶች ፋኖን ቅዱስ አድርገው ሲያቀርቡት ሌሎች ደግሞ እርኩስ አድርገው ያቀርቡታል። አንዳንዶች ከፋኖ ጋር ያለው ልዩነት በሰላም ይፈታ ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ ፋኖ ሰላም የማይፈልግ ስብስብ በመሆኑ እርምጃ ይወሰድበት ይላሉ። አንዳንዶች በፋኖ ላይ እርምጃ መውሰጃው ጊዜ አሁን አልነበረም ሲሉ ሌሎች ደግሞ ፋኖ ራሱ በዚህ ጊዜ እርምጃ እየወሰደ እንዴት መንግስት እርምጃ አትውሰድ ይባላል ሲሉ ይሞግታሉ። በእነዚህ ጭቅጭቆች መሃል እየተጎዳ ያለው ህዝቡ መሆኑን ሁሉም ይስማሙበታል።

ፋኖ የኢትዮጵያን ህዝብ ከህወሃት ጭቆና ለማውጣት የከፈለው መስዋትነት አያጠያይቅም። ይሁን እንጅ በፋኖ ስም የተደራጁ ታጣቂዎችም እያደረሱት ያለው ጉዳት አንድና ሁለት የለውም። መንግስት በቅርቡ እርምጃ ለመውሰድ የተገደደው ፋኖ ከልክ ያለፈ እርምጃ መውሰድ በመጀመሩ መሆኑን እኛ በቅርብ ያለን ሰዎች እናውቃለን። ሁሉም የፋኖ አባላት ጥፋት ሰርተዋል የሚል ድፍረት ባይኖረንም፣ በፋኖ ስም የተደራጁ ሃይሎች ስለሚወስዱት እርምጃ ግን መደበቅ አንፈልግም። ትናንት ፋኖን ደግፈን ቆመናል፣ ዛሬ ስህተት ሲሰራ ደግሞ ካልተቃወምነው የሞራል ልዕልናችን ጥያቄ ውስጥ ይገባል።

ፋኖ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓም ዳባት ወረዳ ላይ የፈጸመው ድርጊት በጽኑ የሚወገዝና ህዝብን ከሁለት የሚከፍል አሳፋሪ ድርጊት ነበር። ምንም እንኳ በዕለቱ አርበኛ ማሳፍንትን ለመያዝ በሚል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 4 ፖሊሶች እንደተገደሉ በፌስቡክ ላይ ቢሰራጭም፣ ይህ ግን ፍጹም ሃሰት ነበር።

እንደሚታወቀው መጋቢት 8 ቀን በፋኖና በመንግስት መካከል እርቅ እንደተደረገ ተዘግቦ ነበር። ለእርቁ ምክንያት የሆነው ደግሞ ከዳባት ወደ አጅሬ ጃኖራ መንገድ በሚሰራው ድርጅት ላይ ፋኖዎች ተከታታይ ጥቃት በማድረሳቸው የተነሳ መንግስት እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የሰላሙን መንገድ በመምረጡ ነበር። ይሁን እንጅ ከእርቁ በሁዋላ ከፍተኛ የሆነ ዘረፋና አስገድዶ መድፈር ሁሉ እየተበራከተ መጣ።

የመንገድ ስራ ድርጅቱ በምሬት እቃውን አስረክቦ ለመውጣት ሲያስብ መስተዳድሩ የፖለስ አባላትን ልኮ ለማረጋገት ሞከረ። በእለቱ ማለትም መጋቢት 10 ቀን 4 የፖሊስ አባላት እና 3 የልዩ ሃይል አባላት የኩባንያውን ሰራተኞች አግኝተው መንግስት ከፋኖ ጋር እርቅ ያደረገ በመሆኑ ስራችሁን ስሩ ብለው መክረው ሲመለሱ አረቡር ድንጋይ ላይ ያልተጠበቀ ነገር አጋጥሟቸዋል።

በእያቅጣቸው ከባድ መሳሪያ የደገኑ ፋኖዎች ፖሊሶችንና የልዩ ሃይል አባላቱን የያዙ መኪኖችን እንዳስቆሟቸው የቡድኑ አዛዥ ሊያነጋግራቸው ሲቀርብ ተኩስ በመክፈት ሶስት ፖሊሶችንና ሁለት የልዩ ሃይል አባላትን ገድለዋል። የሚሊሺያ ሃላፊውና ኮማንደሩ ቆስለው አመለጡ ። ይህ ትልቅ ግፍ ነው። የአካባቢውን ህዝብ በእጅጉ ያሳዘነ የጭካኔ እርምጃ ነው።

እነዚህ ፋናዎች ስራቸው በዚህ ብቻ አያበቃም። በግና ፍየል እየዘረፉ ይበላሉ። የመንግስት ስራ ቆሟል በሚባልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። ሁኔታው አስፈሪ ነው። እነዚህ ሰዎች በፋኖ ስም የሚነግዱ ሽፍቶች እንጅ ፋኖዎች ሊባሉ አይገባም።

የፋኖ ጥያቄ መልስ አገኝቶ በሰላም ቢጠናቀቅ የሁላችንም ምርጫ ነው። መንግስትም ራሱን ተመልክቶ ጥያቄቸውን ፈትቶ የአካባቢው ህዝብ በፍጥነት ወደ ስራ ቢመለስ መልካም ነው። ጎንደር ውስጥ ስራ ቀዝቅዟል። አሁን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሲታከልበት ደግሞ ችግሩን ይበልጥ እያባባሰው ነው። ከሁሉም በላይ የፋኖ ድርጊት ህዝቡን ከሁለት እየከፈለው ነውና አንድ ሊባል ይገባል።

ታዛቢዎች ከጎንደር

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: