ሳውድ አረቢያን ጨምሮ የአረብ አገራት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከአገራቸው ሊያስወጡ ነው

(ERF) የተባበሩት መንግስታ ድርጅት ሳውድ አረቢያ 200 ሺ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንን ለማባረር መወሰኗን ተቃውሟል። ‘እስካሁን ድረስ 2 ሺ 870 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ቀናት 200 ሺ የሚሆኑትን ለመመለስ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውስጥ መረጃዎችን ጠቅሶ ማስታወቁን ረዩተርስ ዘግቧል።

ሳውድ አረቢያ ብቻ ሳትሆን፣ ሌሎችም የአረብ አገራት እና የኢትዮጵያ ጎረቤት አገራትም ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት አቅደዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አስተባባሪ የሆኑት ካተሪን ሶዚ በጅምላ ሰዎችን መላክ ቫይረሱ ይበልጥ እንዲሰራጭ የሚያደርገው በመሆኑ አገሮቹ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠይቀዋል። በሳውድ አረቢያ እስካሁን 4 ሺ 934 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል። 65 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በኢትዮጵያ የህዝብ ጤና ኢንስቲትዩት ውስጥ የሚሰሩት ዘውዱ አሰፋ እንዳሉት ኢትዮጵያኖች 300 እና 500 እየሆኑ በአንድ አውሮፕላን ታጭቀው እንደሚላኩና ቁጥራቸውን እየጨመረ መምጣቱን ለረዩተርስ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: