ድንበር መካለሉ ከኮሮና ድል በኋላ ይደርሳል


በኢትዮ – ሱዳን ድንበር መካከል ያለው የመሬት ይገባኛል ውዝግብ በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚፈታ የሱዳን ጋዜጠኞች እየዘገቡ ነው። አውዛጋቢ የሆኑ ለም መሬቶች ለሱዳን ሊሰጡ እንደሆነ ጋዜጦቹ በደስታ ተሞልተው ዘግበዋል። ከኢትዮጵያ በኩል እስካሁን የተሰማ ነገር የለም። ይህ መረጃ እውነትም ሆነ አልሆነ፣ የመሬት ማካለሉ ሂደት ከኮሮና ድል በሁዋላ መካሄድ እንዳለበት እንገልጻለን። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶችን እናቀርባለን፦

አንደኛ፣ ህዝቡ “መሬት ተሰጥቷል አልተሰጠም” እያለ ውዝግብ ውስጥ የሚገባ ከሆነ ፣ በኮሮና ላይ የሚደረገው ዘመቻ በቂ ትኩረት እንዳያገኝ ያደርጋል። በዚህ ሰዓት ሁሉም ግንባር ወደ ኮሮና ብቻ መሆን አለበት። የህዝቡ 100 ፐርሰት ትኩረት ኮሮናና ኮሮና ስለሚያደርሰው ተጽዕኖ መሆን ይገባዋል። የተበታተነ ትኩረት ኮሮናን አያሸንፍም። ፖለቲካችንን ወደ ጎን አድርገን በአንድ አምሳል መዋጋት አለብን።


ሁለተኛ፣ የድንበር ማካለሉን ተከትሎ በአርሶ አደሮች መካከል ግጭት ሊነሳ ይችላል። መንግስት ሙሉ ሃይሉን የአስችኳይ ጊዜ አዋጁን በማስፈጸምና የህዝቡን ሰላምና መረጋጋት በማስጠበቅ ላይ ማዋል ሲገባው፣ አርሶ አደሮች የሚያነሱትን ግጭት ለማብረድ ስለሚያውለው የሃይል መከፋፈል ያጋጥመዋል።


ሶስተኛ መንግስትን የሚቃወሙ ሃይሎች፣ በመንግስት ላይ ተጨማሪ ግፊት መፍጠሪያ አጀንዳ እንዲያገኙና የህዝቡ ልብ እንዲከፋፈል ብሎም ኮሮናን ረስቶ ለአመጽ እንዲነሳሳ ሊገፋፉ ይችላሉ። ይህ ደግሞ በአገሪቱ የሚታየው አለረመራጋጋት ይበልጥ እንዲቀጣጠል ያደርገዋል።


አራተኛ፣ ሁሉም ወገኖች በተረጋጋ መንገድ ስለድርድሩና ስለሚመለሰውም ሆነ ስለሚገኘው መሬት በቂ መረጃ አግኝተው ውይይት ማድረግ አለባቸው። መንግስት ህዝቡን በበቂ ሁኔታ ሳያስረዳ ምንም አይነት መሬት አሳልፎ መስጠት የለበትም ። ከሁሉም በላይ የአካባቢው ህዝብ የመፍትሄው አካል ሊሆን ይገባል።


በእነዚህ ምክንያቶች መንግስት ከሱዳኖች ጋር ተነጋግሮ ለጊዜው የድንበር ማካለሉን ማቆምና ከኮሮና ድል በሁዋላ ለመፈጸም መስማማት አለበት። ይህ ካልሆነ ግን መከፈት በማይገባው ሰዓት አንድ የጦርነት ግንባር እንደከፈተ ሊቆጥረው ይገባል። ይህ ይዞት የሚመጣውን ጣጣም ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለበት። በተለይ የአማራ ክልል ከፋኖ ጋር ያለበት ውዝግብ አልበቃው ብሎ ተጨማሪ የውዝግብ ግንባር እንዳይከፈት በፌደራል መንግስት ላይ ጫና ማድረግ ይገባዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

Blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: