አገር በፌስቡክና በሽፍታ አይመራም

የኢትዮጵያ ህዝብ በሶስት ሃይሎች እየተመራ ነው። አንደኛው መሪ መንግስት ነው። መንግስት ገና በህዝብ የተመረጠ ባይሆንም፣ በአጋጣሚ በያዘው ስልጣን አገር እየመራ ይገኛል። ከምርጫው በሁዋላ እውነተኛ መንግስት ይኖረናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ሌላው አገር መሪ ደግሞ የጫካና የከተማ ሽፍታ ነው። በአገራችን በእያቅጣጫው ሽፍታ አገር እየዘረፈና ሰው እየገደለ ህዝብን እያማረረ ይገኛል። በጎንደር በፋኖ ስም የሚንቀሳቀሱ ሽፍቶች፣ ህዝብን ቁምስቅሉን እያሳዩት... Continue Reading →

እምነትን ፈተና ላይ የጣለው ኮሮና

የሰው ልጅ እምነት ወይም ሃይማኖት የሚፈተነው አደገኛ በሽታ ሲከሰት ነው። አንዳንዱ እኔ የማመልከው ፈጣሪ ያድነኛል ብሎ ሙሉ እምነቱን ወደ ፈጣሪው ያደርጋል። ሌላው ደግሞ  ሳይንስ የሚለውን መከተል ይመርጣል። እንደ ኮሮና ቫይረስ አይነት አደገኛ ወረርሽኝ ሲመጣ ሰዎች “ ወደ ክሊኒክ ልሂድ ወይስ ወደ ቤተ ክርስቲያን?” በሚል እምነትን በሚፈታተን ጥያቄ ይወጠራሉ። በአውሮፓ ብዙ ሰዎች ሃይማኖታቸውን እየተው ሳይንስን መከተል... Continue Reading →

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ተገኘ

( ERF) በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ የጃፓን ተወላጅ ላይ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ በሽታ መገኘቱን ከንቲባ የጤና ጥብቃ ሚኒስትር አረጋግጡ። ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት ጃፓናዊው ዜጋ ወደ አገር ውስጥ በገባ በ 5ኛው ቀን በሽታው እንዳለበት በኢትዮጵያውያን የላብራቶሪ ሰራተኞች ተረጋግጧል። ከግለሰቡ በቆይታው ሊያገኛቸው ይችላሉ የተባሉ 25 ሰዎች ክትትል እየተደረገባቸው ነው። ዶ/ር ሊያ ህብረሰተቡ እንዲረጋጋ ጠይቀዋል።

አንድ ኢትዮጵያዊ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፈ

( ERF) ጣሊያን ውስጥ አንድ ኢትዮጵያዊ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፎአል። የሟቹ ባለቤት በበሽታው የተያዘች ቢሆንም፣ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ይገኛል። የኢትዮጵያዊው ማንነት በውል አልታወቀም። ጣሊያን ውስጥ በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው። የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት መሰራጨቱ በመላው አለም ስጋትን ደቅኗል። በርካታ አገሮች ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ህዝብ በብዛት የሚገኝባቸውን የስፖርትና የሙዚቃ ዝግጅቶችን እየሰረዙ... Continue Reading →

ኖርዌይ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አሰረች

(ERF) ኖርዌይ ከአለፈው ሳምንት ወዲህ ከ 25 በላይ ኢትዮጵያውያንን አስራ ወደ አገራቸው ልትሸኝ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትም የኖርዌይ መንግስት ኢትዮጵያውያኑን ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚያስችለውን ፈቃድ የሰጠ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሰዎቹን ለማጓጓስ ተስማምቷል ። እርምጃው አለማቀፍ ህግን የሚጣረሰ ተደርጎ የሚታይ ነው ይላሉ ባለሙያዎች።በግዳጅ ከሚመለሱት መካከል ከ 14 አመታት በላይ የቆዩ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል።

WHO declares Coronavirus a global pandemic

(ERF) The World Health Organization finally declared Corona virus has become a global pandemic on Wednesday. Chief of WHO, Tedros Adhanom Ghebreyus said “ “Pandemic is not a word to use lightly or carelessly. ” More than 100 countries in six continents have recorded the emergence of the virus which forced the WHO to declare... Continue Reading →

መንግስት በኦሮምያ ያለው የኢንተርኔት አፈና እንዲያቆም ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ

(ERF)አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ባወጣው መግለጫ በኦሮምያ ክልል ላለፉት 2 ወራት ኢንተርኔት እና ስልክ እንዲቋረጥ መደረጉ አግባብ አይደለም። አፈናው ነዋሪዎች እንደ ልብ እንዳይገናኙ፣ ህይወታቸውን በአግባቡ እንዳይመሩና ከመረጃ ውጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ስል ድርጅቱ ወቀሳ አቅርቧል። በምዕራብ ኦሮምያ ቄለም ወለጋ፣ በምዕራብ ወለጋ  እና በሆድሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን እና በምስራቅ ወለጋ የስልክ መስመሮችና ኢንተርኔት ተቋርጧል። በአንዳንድ ዋና ዋና... Continue Reading →

ዶ/ር አብይ አሕመድ በሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙክራ አወገዙ

( ERF)ጠ/ሚኒስትር አብይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ድርጊቱን አውግዘው፣ “እንዲህ ያሉ ክሥተቶች የሱዳንን መረጋጋትና የለውጥ ጉዞ ሊያደናቅፉ አይገባም።” ብለዋል። ጠ/ሚኒስትር አብይ በሱዳን የተሳካ የሽግግር ስርዓት እንዲፈጠር እገዛ ማድረጋቸው ይታወቃል። የሱዳን መንግስት ከአባይ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያና ግብጽ ጋር በሚደረገው ድርድር ከኢትዮጵያ ጎን በመቆሙ ከአረብ አገራትና ከግብጽ መንግስት ትችትን ሲያስተናግድ ሰንብቷል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ለሱዳን መንግስት... Continue Reading →

Blog at WordPress.com.

Up ↑