እውን ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ደብቃለች?

(ERF) በርካታ ኢትዮጵያውያን የኮሮና ቫይረስ ተሸካሚ ህሙማን ቁጥር እንዴት አነስተኛ ሆነ እያሉ በመጠየቅ ላይ ናቸው። ጥያቄውን የሚያቀርቡት ደግሞ ከህክምና ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ አንዳንድ ሃኪሞችም ይገኙበታል። ታዲያ ጥያቄው ተገቢ በመሆኑ በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ ሃኪሞችን አነጋግረናል። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ የአለም የስብሰባ ማዕከልና የቱሪዝም መዳረሻ ከሆኑ ጥቂት አገራት መካከል አንዷ ናት። በዚህም በርካታ የውጭ ዜጎች... Continue Reading →

“ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ፌስቡክ ያገነነው ጦር መርቶ የማያውቅ ሰው ነው ሲሉ” ጓደኛው ተናገሩ

(ERF) የብ/ጄ አሳምነው ጽጌ የቅርብ ጉዳኛ የነበሩትና ከዚህ ቀደም በመፈንቅለ መንግስት ተጠርጥረው 2 ጊዜ ለእስር የተዳረጉት ጄ/ል ተፈራ ማሞ፣ አሳምነው የኢህአዴግን ሰራዊት ዘግይቶ የተቀላቀለ ጦር መርቶ የማያውቅ ሰው ነበር ሲሉ ለአንድ የአማራ ሚዲያ ተናግረዋል። "አሳምነው ጦር አልመራም ስራው ሰዎችን ማደራጀት ነበር" ሲሉ ጄ/ል አሳምነው በቂ ወታደራዊ ልምድ እንዳልነበረውም ተናግረዋል። አሳምነው አቅዶ መስራት የማይችል፣ በክልሉ ለተፈጠረው... Continue Reading →

ከኮሮና ጋር ተያይዞ የጥላቻ ንግግሮች ቀንሰዋል

(ERF) የኮሮና በሽታን ተከትሎ በኢትዮጵያ ይታዩ የነበሩ የጥላቻ ንግግሮች መቀነሳቸውን መረጃዎች አመለከቱ። የጥናት ክፍላችን ባደረገው የዳሰሳ ቅኝት ከብሄርና ከፖለቲካ ጋር ተያይዞ ይቀርቡ የነበሩ የጥላቻ ንግግሮች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል። የብሄር ፖለቲካን ዋና አጀንዳቸው አድርገው የተለያዩ የጥላች ንግግሮችንና ልዩነቶችን ሲጽፉ የነበሩ የማህበራዊ አክቲቪስቶች አብዛኛው ጽሁፋቸው በኮሮና በሽታ ላይ ማተኮሩን ቅኝቱ ያሳያል። በአማካኝ በፌስቡክ ይቀርቡ የነበሩ አንዱን ወይም... Continue Reading →

ኮሮናን በባህላዊ መድሃኒት

ሰሞኑን ለኮሮና በሽታ አገር በቀል በሆኑ ወይም በተለምዶ ባህላዊ መድሃኒቶችን ለመጠቀም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መገለጹን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። አንዳንዱ “አበጃችሁ’ ሲል ሌላው “አታሹፉ” ብሏል። ምንም እንኳን ዘመናዊው መድሃኒት ከባህላዊ መድሃኒቶች ተነስቶ ያደገ ቢሆንም፣ በዘመናዊ ትምህርት ያደጉ የኢትዮጵያ ልጆች ባህላዊ መድሃኒቶችን ለመጠቀም አይደፍሩም ብቻ ሳይሆን፣ መድሃኒቱን የሚቀምሙትን ሰዎች... Continue Reading →

ኢትዮጵያ ውዝግብ የሚያስነሳ የውሃ ሙሌት አማራጭ ይፋ አደረገች

(ERF) የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው ይፋ ያደረጉትን የውሃ አሞላል ሰነድ በመዳሰስ ሪፖረተር ዘገባ ያቀረበ ሲሆን፣ ሰነዱ ብዙ አወዛጋቢ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን ይዟል። በኢትዮጵያ በኩል የቀረበው አማራጭ የግድቡን የውሃ ሙሌት ሂደት በሁለት ምዕራፍ የሚከፍል ሲሆን፣ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ከ 2 እስከ 5 አመታትን እንደሚወስድ ይገልጻል። በዚህ አመት 4 ቢሊዮን 900 ሚሊዮን... Continue Reading →

ጥርጣሬዎችን ሁሉ በስራ የሚያፈርስ ከንቲባ

ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆኖ ሲሾም ብዙ ጫጫታዎች ነበሩ። “የኦነግ አጀንዳ ተሸካሚ ነው፤ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት የሚል አመለካከት አለው፤ የአዲስ አበባን መስተዳድር ስልጣን በኦሮሞዎች ብቻ አስያዘው፤ መሬት ለኦሮሞዎች እየሸነሸነ ሰጠ፤ ቄሮን አደራጅቶ በባልደራስ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አስደረገ” የሚሉና ሌሎችም ወንጀሎች ይቀርቡበት ነበር። “ታከለ ኡማ የኦነግ ጎማ” እየተባለ በየስብሰባው ተወግዟል። ታከለ ስልጣን ይልቀቅ የሚሉ... Continue Reading →

የኮሮና ቫይረስ መድሃኒት ሙከራ

( ERF) የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ት ቴዎድሮስ አድሃኖም ታሪካዊ ያሏቸውን መድሃኒቶች ለመሞከር በኖርዌይና ስፔን ፈቃደኛ የሆኑ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን መመዝገብ መጀመራቸውን አርብ እኤአ 28/03/2019 አሳውቀዋል። ለሙከራ የቀረቡት መድሃኒቶች የትኞቹ ናቸው? ነባሮቹ ወይስ አዲሶቹ? ውጤታቸውስ እንደታሰበው ይሳካ ይሆን? ክትባት የአለም የጤና ድርጅት (WHO) በቻይና ውሃን ከተማ ሳንባን የሚያጠቃ ያልታወቀ በሽታ መከሰቱን እኤአ በ31 December... Continue Reading →

የአለም የጤና ድርጅት ዛሬ ታሪካዊ ያለውን የ ኮሮናን መድሃኒት ሙከራ ይጀምራል

(ERF) የአለም የጤና ድርጅት መሪ ዶ/ር ቲዎድሮስ አድሃኖም በሰጡት መግለጫ ዛሬ በኖርዌይና ስፔን አራት አይነት መድሃኒቶች በተመረጡት በሽተኞች ላይ ሙከራ የደረግባቸዋል።የመድሃኒት ሙከራውን ኮረናን ለመከላከል የተወሰደ ታሪካዊ እርምጃ መሆኑን በደስታ እገልጽላችሁዋለሁ ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ፣ ሌሎች 45 አገራትም በተመሳሳይ መንገድ ሙከራ ለማካሄድ ፈቃደኝነታቸውን ገለጸውልናል ብለዋል። ሌሎችም አገሮች በፍጥነት ሙከራውን ካካሄዱ፣ የመድሃኒቱን ውጤታማነት ቶሎ እናውቃለን ሲሉ አክለዋል።ዶ/ር ቴዎድሮስ... Continue Reading →

የሃይማኖት ተቋማትን ባንኮችንና ሃኪሞችን በተመለከተ ተጨማሪ ትዕዛዝ ተሰጠ

(ERF) መንግስት  የኮርና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ዛሬ ባወጡት ተጨማሪ መመሪያ ላይ አብያተ ክርስቲያናትና መስኪዶች ሊዘጉ የሚችሉበትን ፍንጭ ሰጥቷል። የፌዴራል መንግሥት አስከፊ ብሔራዊ አደጋ በሚከሰት ጊዜ ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች እንዲቋረጡ የማድረግ ሕገ-መንግሥታዊ መብት አለው የሚለው መመሪያው፣ በሕገ-መንግሥቱ የተደነገጉት እርምጃዎች ተግባራዊ ከመደረጋቸው በፊት ዜጎች አካላዊ ርቀት የመጠበቅን መመሪያ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አዟል። ፌደራል ፖሊስም ህዝቡ አስፈላጊውን እርቀት መጠበቁን እንዲከታተል... Continue Reading →

የቡድን 20 አገሮች ለደሃ አገሮች ድጋፍ ለማድረግ ተስማሙ

(ERF) በአለማችን በኢኮኖሚ አቅማቸው የዳበሩ የቡድን 20 አገራት ዛሬ በሳውድ አረቢያው ንጉስ ሰልማን አማካኝነት የቪዲዮ ኮንፍረስ አድርገዋል። የኮንፈረንሱ ዋና አላማ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ በአለም ላይ የተፈጠረውን ከፍተኛ የኢኮኖሚ መናጋት ለማስተካከል ነው። አገሮቹ ወደ 5 ትሪሊየን የሚጠጋ ገንዘብ ኢንቨስት ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ኮሮናን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የምግብ፣ የመድሃኒትና ሌሎችንም የአቅርቦት ችግሮች ለመከላከልም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።... Continue Reading →

Blog at WordPress.com.

Up ↑